የጋዜጣዊ መግለጫ ይዘት

የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻው (መሪ ቃል)

“ ክለቦቻችንን እንታደግ!! ”

ንኡስ ርእስ

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ታላቅ ሚና የነበራቸው፣ ለብሄራዊ ቡድን ልዩ ተሰጥዖ ያላቸው እና ጠንካራ ተጫዋቾችን ያበረከቱ፣ ለኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ፉክክር ድምቀት የነበሩትን 3ቱ የትግራይ ክልል ክለቦች (መቀለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ እና ስሁል ሽረ) ከመክሰም እናድን መልሰው እንዲቋቋሙ እንደግፍ የሚል በጎ ሃሳብ የያዘ ነው::

የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ዓላማው

  • በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሀገር ደረጃ ተሳታፊ የነበሩ በኢትዮጵያ እግር ኳስ በብሄራዊ ቡድን ታላቅ ሚና ያላቸው 3ቱ የትግራይ ክልል ክለቦች (መቀለ 70 እንደርታ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ እና ስሁል ሽረ) ባለፉት ሶስት ዓመታት ተፈጥሮ በነበረው ጦርነት ምክንያት ክለቦቹ ሙሉ በሙሉ ፈርሰዋል፣ እነዚህን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለፕሪምየር ሊጉ ድምቀት እና መነቃቃትን ፈጥረው የነበሩ ክለቦችን ፈርሰው እንዳይበተኑ ለማድረግ የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ነው።
  • የትግራይ ክልል ስፖርትን ለማነቃቃት እና ህዝቡ በጦርነቱ ምክንያት ከደረሰበት የስነ ልቦና ቀውስ በቶሎ ማገገም እንዲችል ማድረግ ተቀዛቅዞ የነበረውን የስፖርት ውድድር መንፈስ መልሶ ማነቃቃት፣

የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ጥቅሶች

“ ከጦርነቱ ማግስት የትግራይ ስፖርትን መደገፍ፣ ማነቃቃት እና ወደ ነበረበት ለመመለስ
የዜግነት ብቻ ሳይሆን የሕግ እና የሞራል ግዴታችንም ነው::”

ኤፍሬም የማነ (ኢዋይ ፕሮዳክሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ)

“በፊፋ ፌይር ፕሌይ መርህ መነሻነት ስፖርት ዘር፣ ቀለም፣ ሀይማኖት፣ ብሄር ሳይለይ የሚካሄድ ሰላማዊ ጦርነት ነው። በመሆኑም ሰላማዊ ጦርነትን ከአውዳሚ ጦርነት ማስቀደም ምርጫችንም ብቻ ሳይሆን ግዴታችንም ነው።”

መድኃኔ ዘካርያስ (ኢዋይ ፕሮዳክሽን ማርኬቲንግ እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር)

የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ግብ

በሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለይ ተጋሩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን፣ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት፣ኤምባሲዎች ወዘተ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ነው።

በገቢ ማሰባሰቢያው ዘመቻ የሚከናወኑ ተግባራት

  • የገቢ ማሰባሰቢያ Launching Program በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እንዲሁም የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሚታደሙበት ከፍተኛ የመንግስት ሚኒስትሮች እና የስራ ሃላፊዎች፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ፕሬዝዳንቶች፣ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ ሃላፊዎች፣ የክልል መንግስታት ፕሬዝደንቶች፣ የእግር ኳስ ክለብ ማናጀሮች፣ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ አምባሳደሮች፣ታዋቂ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ወዘተ የሚገኙበት መክፈቻ ፕሮግራም ይደረጋል፣
  • ስፖርት በትግራይ ከጦርነቱ በፊት እና በኋላ ያለበትን ሁኔታ የሚያስቃኝ አጭር ዶክመንታሪ ፊልም በመክፈቻው ፕሮግራም ላይ ይቀርባል
  • በ EY Production በሶስቱ የትግራይ እግር ኳሰ ክለቦች ጥምር ፊርማ በሚከፈተው የGo Fund Me Account መሰረት የዩቲዩብ ፔጅ ይከፈታል የዲጂታል ማስታወቂያዎች በተለይዩ ይዘቶች ይዘጋጃሉ ይተላለፋሉ
  • ከገቢ ማሰባሰቢያው መዝጊያ በመቀሌ ከመካሄዱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ስፖርት ጦርነትን ከመቀልበስ እና ሰላምን ከማስፈን አንጻር የአለም ተሞክሮ ምን ይመሰላል የሚል ጥናታዊ ጽሁፍ በመቀሌ ዩንቨርሲቲ መምህራን አቅራቢነት ከስፖርት ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር የፓናል ውይይት በመቀሌ ፕላኔት ሆቴል ይካሄዳል::
  • ከገቢ ማሰባሰቢያው መዝጊያ በመቀሌ ከመካሄዱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ስፖርት ጦርነትን ከመቀልበስ እና ሰላምን ከማስፈን አንጻር የአለም ተሞክሮ ምን ይመሰላል የሚል ጥናታዊ ጽሁፍ በመቀሌ ዩንቨርሲቲ መምህራን አቅራቢነት ከስፖርት ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር የፓናል ውይይት በመቀሌ ፕላኔት ሆቴል ይካሄዳል::

የገቢ ማሰባሰብ ዘመቻ መሪዎች አድራሻ

Ey Production Plc, Addis Ababa, Ethiopia.
E-Mail: ephremyemane@gmail.com

Telephone #:- +251-911800752. Ephrem Yemane (CEO)

Ey Production Plc, Addis Ababa, Ethiopia.
E-Mail: pinumed@gmail.com

Telephone #:- +251-966253564 Medhane Zekarias
(Marketing and Communication Director)

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top