ግንቦት 29፤2016 – ላለፉት አንድ ዓመታት ገደማ ከጦርነት ማግስት ስፖርት በሀገር አንድነት ሰላም እና ታላቅ ማህበራዊ ትስስር ላይ የሚፈጥረውን ታላቅ አሻራ በያዘ መልኩ በተቀናጀ መልኩ ሲከናወን የነበረው የትግራይ ክለቦችን ከመፍረስ ለማዳን ” ክለቦቻችን እንታደግ ” /” ጋንታታና ነድሕን ” / የተሰኘው የገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ የመጨረሻ ምዕራፍ ታላቅ ብሄራዊ ቴሌቶን መሠናዶ ሰኔ 18 በሸራተን አዲስ እንደሚከናወን ተገለፀ ።

ዛሬ በሸራተን አዲስ በተደረገ ጋዜጣዊ መግለጫ የዝግጅቱ የመጨረሻ ምዕራፍ መሰናዶን በተመለከተ የትግራይ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተክላይ ፍቃዱ በታደሙበት መግለጫ ከጦርነት ማግስት የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባቸው የትግራይ ክለቦችን ለማቋቋም ስፖርት ለሰላም ስፖርት ለሀገር አንድነት ለላቀ ማህበራዊ ትስስር ያለውን ታላቅ አቅም ከግብ ያስቀመጠ በጀግነዋ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ክብር አምባሳደርነት ሚና የተመራው የትግራይ ክለቦችን መልሶ ለማቋቋም የተካሄደ በጎ ዓለማን የሰነቀ ዘመቻ በትግራይ ክልል አስተዳደር አስፈፃሚነት ሰኔ 18 በሸራተን አዲስ ላሊበላ አደራሽ በሚኖር ብሄራዊ ቴሌቶን እንደሚፈፀም የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ገልፀዋል ።
በጎውን ታላቅ ዓለማ በመደገፍ ከታሰበለት ግብ ለማድረስ በትግራይ ክልል ርዕስ መስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የቀረበው የትግራይ ክለቦችን በፋይናንስ የማገዝ ሀገራዊ ጥሪን ተከትሎ ክልሎች መንግስታዊ ተቋማት ባለሃብቶች የተለያዩ ወገኖች በርካታ ተቋማት መላው ኢትዮጵያውያን እንደሚሣተፉ ተገልፃል ። ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በሊጉ የነበሩት የትግራይ ክለቦች መልሰው በሊጉ እንዲካፈሉ በቅርቡ በኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተወሰነው ውሳኔን ተከትሎ መቀለ 70 እንደርታ ወልዋሎ እና ስሑል ሽረን በ2017 ዓ.ም የሊጉ ውድድሩር በቀድሞዎ ቀለማቸው ተፎካካሪ ተሳታፊ ለማድረግ የገቢ ማሰባሰቢያው ቴሌቶን ታላቅ የፋይናንስ አቅም እንደሚፈጥር ተነግራል ።
ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ በተለይ የደቀቀው የትግራይ ስፖርት አቅምን ለማጠናከር ለማነቃቃት ሚናው ኋያል እንደሆነ ተገልፃል ። በተለይ በሊጉ ተመልሶ ከመካፈል በዘለለ የውጤት ዓለማ የፍክክር ዝግጁነት ላይ በትግራይ ክልል ስፖርት ኮሚሽን አስተባባሪነት ከክለቦቹ በመነጋገር ከባለድርሻ አካላት በመተባበሮ ተስጦኦዎችን ከመመልመል አንስቶ በማህበረሰቡ ደግም መነቃቃት ታላቅ ሚና መጫወት የቻሉ ውድድሮችን ከሰፊ የፋይናንስ ፈተና ጥያቄዎች ጋር መከናወናቸው ተገልፃል ።
ያለ ሶስቱ የትግራይ ክለቦች ተሳትፎ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮናን የኢትዮጵያ ብሎ መጥራት ፈታኝ ነው ። የትግራይ ክለቦች ወደ ሊጉ የመመለስ አውንታዊ ጥያቄን ተከትሎ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካኝነት ሂደቱን የማስፈፀም ስራ በተቃና መልኩ መከናወኑ ስፖርት በሀገር አንድነት ላይ የሚፈጥረው ታላቅ አሻራ አንዱ ታሪካዊ ማሳያ እንደሆነም በመግለጫው ተጠቅሷል ።
የትግራይ ክለቦች ወደ ሊጉ ከመመለስ በዘለለ በሊጉ ለሚጠብቃቸው ቻሌንጅ ዝግጁነት ክለቦቻችንን እንታደግ በሚል መሪ ቃል ከጦርነት ማግስት ግጭት ጦርነት ማንን ጠቀመ ? ስፖርት የሰላም መሣሪያ የአንድነታችን አቅም ዋና መሠረት ሆኖ ያለውን ታላቅ አቅም በማስተባበር ” በእናንተ ውስጥ እኛም አለን … የተሰኘው ብሄራዊ ቴሌቶኑን በስኬት በታቀደለት ግብ ለማስፈፀም የትግራይ ክልል አስተዳደር ከዝግጅቱ አስተባባሪዎች በተቀናጀ መልኩ ለመጨረሻው ምዕራፍ ዝግጅት እየተሰራ መሆኑን በመግለጫው የታደሙት የትግራይ ክልል ስፖርት ከሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተክላይ ፍቃዱ ይፋ አድርገዋል ።

በትግራይ ክልል በኩል የትግራይ ክለቦችን በፋይናንስ ለማጠናከር ጥሪ የሚደረገሰላቸው ወገኖች ሁሉ ሰኔ 18 በሸራተን አዲስ በሚካሄደው ብሄራዊ ቴሌቶን የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪም ተላልፏል ።

” ክለቦቻችን እንታደግ ”
በእናንተ ውስጥም እኛም አለን …
ስፖርት ለሰላም ስፖርት ለፍቅር ስፖርት ለሀገር አንድነት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top