My Game is Fair play !

My Game is Fair play !
አሚጎ ፓራ ሴምፔሬ …
ፍቅር ዳርቻ የለውም ። ጓደኝነታችን ወዳጅነታችን የዘለዓለም ነው  የክረምትና የበጋ አይደለም ። ተራርቀን እንኳን አንድ ላይ ነን ። ይቺን ዓለም የምንጋራ ፍጡራን ! የማይረሱ ታሪኮችን የፃፍን !
ገና ብዙ የሚጠብቀን !  አንድ ስንሆን ከፍታችን የላቀ ነው ።
ስንተጋገዝ ስንረዳዳ በጋራ ስንቆም እንገዝፋለን ። ከሚያላያየን የሚያቀራርቡን ነገሮች እልፍ ናቸው ። ህይወት በአንድነታችን ውስጥ ውበት ናት ። አሚጎስ ፓራ ሴምፔሬ  …

” ክለቦቻችን እንታደግ ”  በሚል መርህ ከጦርነት ማግስት ሊፈርሱ የተቃረቡ የትግራይ ክልል የስፖርት ክለቦችን በመታደግ  ስፖርት ያለውን ታላቅ ማህበራዊ ትስስር የመፍጠር አቅምን  ለማሳየት በተጀመረው በጎ ዓለማን የሰነቀ ዘመቻን ከግቡ ለማድረስ  ey production መቀለ ትግራይ መቀመጫውን ካደረገው  ናይና ስፖርት ጋር በጣምራ ለመሥራት ስምምነት ፈፅሟል ።

My Game is Fair play ! አሚጎስ ፓራ ሴምፔሬ  ! ስፖርት ለሁሉም ! ስፖርት ለሰላም !  ለሀገር አንድነት ! በኢትዮጲያ የስፖርት እንቅስቃሴ ታሪክ በዘመን ቅብብል በፁናት የጀገኑ ውጤታማ ስፖርተኞችን በማፍራት የሀገር ወገን ኩራት ሆነው ኋያል አሻራ የተወጡ ዛሬ  ከጦርነቱ ማግስት የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባቸው የትግራይ ክልል ክለቦችን  ለመታደግ
ey production ከናይና ስፖርት  ጋር በአንድነት ከጀመሩት የተቀናጀ ማህበራዊ ሚና ጎን እንዲሰለፉ ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን ። አሚጎስ ፓራ ሴምፔሬ ! My Game is Fair play …

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top